Minnesota Secretary Of State - በምርጫው ቀን መምረጥ (Election Day Voting)
Skip to main content

በምርጫው ቀን መምረጥ (Election Day Voting)


በዚህ ገጽ፡ የት እንደሚመርጡ፡ ወደ ምርጫው ጣብያ ምን ማምጣት እንደምትችሉ፡ እርዳታ ማግኘት እንዴት እንደምትችሉ፡ የመራጭ መብትዎ ምን እንደሆነ ተረዱ።

የምርጫ ቦታዎችና ሰዓታት

የት ሂደው እንደሚመርጡ እውቁ ኣብዛኛዎቹ የምርጫ ጣብያዎች ከ 7 a.m. እስከ 8 p.m (በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ከጥዋቱ 1 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት) ክፍት ሁነው ይቆያሉ።

ምን ማምጣት እንደሚቻል

የተመዘገቡት በወቅቱ ካሉበት ኣድራሻ ከሆነ፡ የመታወቅያ ወረቀት ማምጣት ኣያስፈልጎትም።መመዝገብ ከፈለጉ ወይም የተመዘገቡትን ማሻሻል ከፈለጉ ግን የሚከተለውን ማሳየት ያስፈልጎታል ክመምረጥዎ በፊት፡ የኣድራሻ ማረጋገጫ

ሲመርጡ እርዳታ ያግኙ

በሚመርጡበት ወቅት፡ እርዳታ ለማግኘት የሚያስችልዎ ብዙ መንገዶች ኣሉ።እንዲረዳዎት ሌላ ሰው ማምጣት፡ የኣስመራጭ ኮሚቴውን ዳኛ መጠየቅ፡ በምርጫዎ ላይ ምልክት ለማድረግ የሚያስችልዎ መሳርያ መጠቀም፡ ወይም መኪናዎ ውስጥ ሁነው መምረጥ

የቤተሰብ፡ የጓደኞች ወይም የጎረቤቶች እርዳታ

በምርጫው፡ እርዳታ ለማግኘት ማንንም የቤተሰቦ ኣባል፡ ጓደኛዎን፡ጎረቤትዎን ወይም ማንኛውንም የመረጡትን ሰው ይዘው መምጣት ይችላሉ። ይህ ሲባል ግን የስራ ኣለቃዎን፡ የሰራተኞች ማህበር ሃላፊዎንና የምርጫው ዕጩ የሆነን ሰው ለማምጣት ኣይፈቀድም።

የሚያግዞ ሰው፡ በሁሉም የምርጫ ሂደቶች ውስጥ፡ ወደ ምርጫ ኪዮስኩም ጭምር ኣብሮ በመግባት፡ ሊያግዞት ይችላል። ይሁንና፡ ኣጋዦች፡ በኣንድ የምርጫ ወቅት፡ በሶስት መራጮች ምርጫዎች ላይ ብቻ ነው በኣካል ተገኝተው ምልክት በማድረግ ሊያግዙ የሚችሉት። የመረጡት ሁሉ፡ በትክክል ምልክት እንደተደረገበት ለማረጋገጥ የምርጫ ወረቀትዎን ለኣስመራጭ ኮሚቲው ዳኛ በሚስጢር ማሳይትም ይችላሉ።

ኣጋዦች፡ በምርጫዎ ላይ ጫና ሊያደርጉ ኣይችሉም። እንዲሁም ማንን እንደመረጡ ለሌሎች መንገር ኣይችሉም።

የመንገድ ዳር ምርጫ

ወደ ምርጫ ጣብያው ለመግባት፡ ከመኪናዎ በቀላሉ መውጣት የማይችሉ ከሆነ፡ የምርጫው ወረቀት መኪናዎ ድረስ እንዲመጣልዎ መጠየቅ ይችላሉ። ይህም የመንገድ ዳር ምርጫ (curbside voting.) በመባል ይታወቃል።

ክተለያዩ ዋነኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች፡ ሁለት የኣስመራጭ ኮሚቴው ዳኞች የምርጫ ወረቀቶችን ይዘው ወዳሉበት መኪና ያመጡሎታል።በወቅቱ ለመመዝገብም ከፈለጉ ወይም የተመዘገቡበትን ለማሻሻል ከፈለጉ፡ የማመልከቻ ፎርሙንም ይዘውሎት ይመጣሉ።

ምርጫዎን ከጨረሱ በውሃላ፡ የኣስመራጭ ኮሚቴው ዳኞች፡ የምርጫውን ወረቀት ምርጫው ጣብያው ውስጥ በማምጣት በምርጫ ሳጥኑ ውስጥ ይከቱታል።

የምርጫ ምልክት የሚያደርግ መሳርያ እርዳታ

ኣብዛኛዎቹ የምርጫ ጣብያዎች፡ በመረጡት ላይ ምልክት የሚያደርግ መሳርያ ኣላቸው።ብዕር መጠቀም ካልፈለጉ ወይም ብዕር መጠቀም ካልቻሉ፡ ይህንን መሳርያ መጠቀም ማንን እንደመረጡ እንዳይታወቅ ሚስጢራዊነት ይሰጦታል።

ይሄው መሳርያ፡ በምርጫ ወረቀትዎ ላይ ያለውን ጽሁፍ በትልቁ የሚያሳይ ወይም በስተጀርባ ከሚገኘው ቀለም ጋር ኣወዳድሮ በጥሩ ሁኔታ እንዲታይ የሚያደርግ ችሎታ ኣለው። በድምጽ ማጉያ መሳርያም የምርጫ ወረቀቱን ሊያነብሎት ይችላል።

ዓይነ ስውራን እንዲያነቡበት በተዘጋጀ በብሬል፡ በታችስክሪን(touchscreen) ወይም በ sip-and-puff device፡ ትንፋሽን ወደ ውስጥና ወደ ውጭ ሲተነፍሱበት መጻፍ በሚችል መሳርያ የምርጫ ወረቀትዎን ሊሞሉ ይችላሉ። ምርጫዎን ከጨረሱ በውሃላ። የምርጫ ወረቀትዎን ሙሉ በሙሉ ኣትሞ ይሰጥዎታልሉ።

ከኣስመራጭ ኮሚቴ ዳኞች የሚገኝ እርዳታ

የኣስመራጭ ኮሚቴ ዳኞች ፡ በቦታው የሚገኙት በምርጫው ሂደት ሁሉ እርዳታቸውን እንዲሰጡ ነው።

በምርጫ ወረቀትዎ ላይ ምልክት ለማድረግ እርዳታ የሚያስፈልግዎ ከሆነ፡ ከተለያዩት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁለት ዳኞች ሊረዱ ይችላሉ። እነኚህ ዳኞችም፡ በሚያድርጉት ምርጫ ላይ ጫና ሊያደርጉ ወይም ማንን እንደመረጡ ለማንም መንገር ኣይችሉም።

ለመምረጥ ከስራ ፈቃድ ስለማግኘት

ከደሞዝዎም ሆነ ከግል የፈቃድ ግዜዎና ከእረፍት ቀናትዎ ምንም ሳይቆረጥ፡ በክፍለ ሃገሮ፡ በኣገሪቱ ጠቅላላ ምርጫና ቀናቸው በታወቀ በመደበኛ የኣካባቢዎ ምርጫዎች ላይ ሂዶ ድምጽዎን የመስጠት መብት ኣሎት።

የምርጫው ግዜ በስራ ሰዓትዎ ከሆነ፡ ሂዶ ለመምረጥ ለሚያስፈልግዎ ግዜ፡ ኣሰሪዎ ሊከፍሎት ይገባል።ኣሰሪዎ፡ የግል የፈቃድ ግዜዎን ወይም የእረፈት ግዚዎን እንዲጠቀሙ ሊጠይቅ ኣይችልም።(የሚኖሶታን ሕገመንግስት 204C.04 and 204C.08 Subd.1d)ይመልከቱ።

ሂዶ ለመምረጥ የሚያስፈልጎትን ግዜ ብቻ ወስደው ወደ ስራ ቦታዎ ተመለሱ።

ይህንን መብት በተመለከተ፡ኣሰሪዎ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እምቢ ማለት፡ ግዜውን መቀነስ ወይም ጣልቃ መግባት ኣይችልም። በዚህ ሰዓት ሂደው ይምረጡ በማለትም የሚመርጡበትን ሰዓት ሊወስን ኣይችልም።

ኣሰሪዎ ለመምረጥ የሚሄዱበት ሰዓት መቼ እንደሆነ ሊጠይቅዎ ይችላል። እንዲሁም ሊያስከትል የሚችለውን የስራ እንቅፋት ለመቀነስ፡ ሰራተኞች ለመምረጥ የሚሄዱበት ሰዓት የሁሉም ኣንድ ላይ እንዳይሆን እንዲያስተካክሉ ሊጠይቅ ይችላል።

ሂደው የሚመርጡበት ግዜ በነጻ እንዲሰጥዎ መብት እንዳሎት የሚያስረዳውን የዚህን ጽሁፍ ግልባጭ ለኣሰሪዎ መስጠት ይችላሉ።

ይህንን መብት የጣሰ ኣሰሪ፡ ቀላል ወንጄል በመፈጸም በደለኛ ይሆናል። ማንኛውም ከሰራተኞች የሚቀርብ ቅሬታ በኣውራጃው ጠበቃ ጽህፈት ቤት ውስጥ በፋይል ይያዛል።

መብቶችዎን ይወቁ

እንደ ኣንድ የሚኖሶታ መራጭ ኣያሌ መብቶች ኣሎት- ሁሉንም እወቅዋቸው'

  • ከስራ ቦታዎ ወጥተው ለመምረጥ ነጻ ግዜ ኣግኙ

    ከደሞዝዎም ሆነ ከግል የፈቃድ ግዜዎና ከእረፍት ቀናትዎ ምንም ሳይቆረጥ ሂዶ፡ ከስራ ቦታዎ ወጥተው ድምጽዎን የመስጠት መብት ኣሎት።

  • በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት ድረስ (8 p.m.) ሰልፍ ላይ ካሉ መምረጥ ይችላሉ።

    በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ከምሽቱ ሁለት ሰዓት (8 p.m)በፊት ሰልፍ ላይ ካሉ የመምረጥ መብት ኣሎት።

  • በምርጫው ቀን ስለመመዝገብ

    በምርጫው ቀን ለመምረጥ በዕለቱ ዕለት ተመዝግበው የመምረጥ መብት ኣሎት፡ ይህም የሚከተለውን ካሳዩ ነው ኣስፈላጊው የመኖርያ ቤት ኣድራሻ ማረጋገጫ

  • በቃል ፈርሙ

    ስምዎን መፈርም ካልቻሉ፡ ማን መሆንዎን በቃል የማረጋገጥና ሌላ ሰው እንዲፈርምሎት የማድረግ መብት ኣሎት።

  • እርዳታ ይጠይቁ

    ከኣሰሪዎ ወኪል ወይም ከሰራተኞች ማህበር ተጠሪ ወይም ከምርጫው ዕጩ በስተቀረ፡ የማንንም እርዳታ የመጠየቅ መብት ኣሎት።

  • ልጆችን ወደ ምርጫው ጣብያ ማምጣት

    ልጆችዎን ወደ ምርጫው ጣብያ የማምጣት መብት ኣሎት።

  • ወንጄል የፈጸሙበትን ቅጣት ከፈጸሙ በውሃላ መምረጥ

    ወንጄል የፈጸሙበትን ቅጣት ሙሉ በሙሉ ከፈጸሙ በውሃላ፡ ከእስር ቤት ለግዜው እንዲወጡ የተደነገገቦትን የቀናት ገደብ ካጠናቀቁ በውሃላ ወይም የተጠይቀ ካሳ ካለ እሱን ከከፈሉ በውሃላ ለመምረጥ ይችላሉ።

  • በሰው ጥበቃ ስር እያሉ መምረጥ

    የመምረጥ መብትዎ በዳኛ ካልተገፈፈ በስተቀረ፡ በሰው ጥበቃ ስር ቢሆንም ፡ የመምረጥ መብት ኣሎት

  • ካለ የማንም ሰው ማግባባት ምረጡ

    በምርጫ ጣብያው ውስጥ፡ ማንም ሰው በምርጫዎ ላይ ማናቸውንም ዓይነት ጫና ሳያደርግብዎ የመምረጥ መብት ኣሎት።

  • ኣዲስ ተተኪ የምርጫ ወረቀት ያግኙ

    ስህተት ካደረጉ፡ በምርጫ ሳጥኑ ውስጥ የምርጫ ወረቀትዎን ከመክተትዎ በፊት፡ ሌላ ኣዲስ የምርጫ ወረቀት እንዲሰጥዎ መጠየቅ መብትዎ ነው።

  • ቅሬታ ማቅረብ

    የምርጫው ሁኔታ/ኣካሄድ ካላስደስትዎ፡ ቅሬታዎን በጽሁፍ ለምርጫ ጣብያዎ ማቅረብ መብትዎ ነው።

  • ለዓይነት የሚሆንዎ የምርጫ ወረቀት ማምጣት።

    ወደ ምርጫው ኪዮስክ ውስጥ፡ ለዓይነት የሚሆንዎ የምርጫ ወረቀት የማምጣት መብት ኣሎት።

  • የመራጭ መብቶች ዝርዝር ህጎች (Voter’s Bill of Rights) የጽሁፍ ግልባጭ ወደ ምርጫ ኪዮስኩ ይዞ መግባት መብትዎ ነው።

    የመራጭ መብቶች ዝርዝር ህጎች (Voter’s Bill of Rights) የጽሁፍ ግልባጭ ወደ ምርጫ ኪዮስኩ ይዞ መግባት መብትዎ ነው (የሚኖሶታ ህገ መንግስት ኣንቀጽ 204ሲ፡ 08፡ ክፍል. 1ቢ- Minnesota Statutes 204C.08, subd. 1b)