ግዜው የሞርጫ ዋዜማ ነው! የምርጫ ካርድ ደርሶውታል? በአስቸኳይ እዲመልሱ በእክብሮት እንጠይቆታለን::
በፗስታ እንዳይመልሱ አጥብቀን እንገልጻለን::
ምርጫዎን በአከባቢዎ በሚገኘው የመምረጫ ቢሮ በአካል በመገኘት መምረጥ እዳለቦት በአክብሮት እናሳስባለን::
ድምፆ ለመቆጠር እዲይችል የምርጫ ካርድዎን በነገው እለት ታህሣሦ 3 ቀን መግባት ይኖርበታል ::
የምርጫው ቀን ከመድረሱ በፊት ባሉት 45 ቀናት ውስጥ በምርጫ ወረቀትዎ መምረጥ ይችላሉ።
በኣካል ተገኝተው ለማይመርጡ ወይም ከምርጫው ቀን በፊት ለመምረጥ ለሚፈልጉ የሚላክ የምርጫ ወረቀት በፖስታ እንዲላክሎት ማመልከት ይችላሉ። ይህንንም የምርጫ ወረቀት ሞልተው የምርጫው ቀን ከመድረሱ በፊት እንዲደርስ ይላኩ።
የምርጫ ፎርሙን በሚሞሉበትና በሚያጠናቅቁበት ወቅት፤
ምስክር ያስፈልጎታል። ይሄው ምስክር፤ የሚኖሶታ የተመዘገበ መራጭ ወይም ለመመስከር በመንግስት ፍቃድ የተሰጠው ወኪል መሆን አለበት። ይሄው ምስክር፤ በፖስታው በሚታሸገው ፎርም ውስጥ ላይ መፈረምና አድራሻውን መጻፍ አለበት።
ልክ የምርጫ ፎርሙን ሞልተው እንደጨረሱ፤ ወድያውኑ ይላኩት። ከፈለጉም የምርጫ ፎርሙን ወደላከሎት መስርያ ቤት በአካል ሂደው የሞሉትን የምርጫ ፎርሞን ለመስጠት ይችላሉ።
በተጠየቀው ግዜ የሚደርሱና በትክክል የተሞሉ ፎርሞችን የያዙ የምርጫ ወረቀቶች ይቆጠራሉ።
የምርጫ ወረቀትዎ ሁኔታ ምን እንደሆነ ተከታተሉ። እንደተቀበሉትና እንደተቆጠረም ኣረጋግጡ