በዚህ ገጽ ላይ ማን መምረጥ እንደሚችልና ከዋናው የምርጫ ቀን በፊት እንዴት መመዝገብ እንደሚችሉ ተረዱ
በሚኖሶታ ውስጥ ለመምረጥ፡ የኣሜሪካን ዜጋ መሆን ኣለብዎ፡ በምርጫው ዕለት ቢያንስ ቢያንስ ዕድሜዎ 18 ዓመት መሆን ኣለበት፡ በሚኖሶታ ውስጥ ቢያንስ ቢያንስ 20 ቀናት የተቀመጡ መሆን ኣለብዎ።
ከባድ ወንጀል ፈጽመው የተቀጡ ከሆነ፡ በፍርድቤት የተፈረድቦትን ፍርድ ሙሉ በሙሉ ካጠናቀቁ በውሃላ ብቻ ነው መምረጥ የሚችሉት። ይህም ግዚያዊ ከእስር የመለቀቅን፡ እንዲሁም በኣንዳች ስምምነት ከእስር የመውጣትን ግዜንና ካሳ ክፍሎ የማጠናቀቅ ሁኔታንም ይመለከታል።
በፍርድ ቤት የመምረጥ መብትዎ ካልታገደ በስተቀረ፡በሰው ጥበቃ ስር እያሉም ለመምረጥ ይችላሉ።
ለመምረጥ በወቅቱ ባሉበት ኣድራሻ የተመዘገቡ መሆን ኣለቦት። በኦንላይን፡ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ለመምረጥ ተመዝገቡ። ወይም በኣማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ የጽሁፍ ፎርም ማተም ይችላሉ።
በምርጫው ዕለትም ወደ ምርጫ ጣብያዎ በመሄድ መመዝገብ ይችላሉ የስምዎንና የወቅታዊ ኣድራሻዎን ማረጋግጫ ማሳየት ኣለብዎ።
ኣድራሻዎን በቀየሩ ቁጥር፡ ወይም ስሞን ሲቀይሩ ወይም በ4 ዓመታት ውስጥ ኣንዴም ቢሆን ካልመረጡ፡ እንደገና መመዝገብ ያስፈልጎታል። ኣዲስ የምርጫ ምዝገባ ፎርም በመጠቀም፡ ምዝገባዎን ያድሱ ወይም ያሻሽሉ።
በምርጫው ቀን፡ በምርጫ ጣብያዎ ለመመዝገብ ከታች ከተዘረዘሩት ማረጋገጫዎች ኣንዱን ማምጣት ኣለብዎ
1. ወቅታዊ ስምዎና ኣድራሻዎ ያለበት የመታወቅያ ወረቀት
2. ፎቶግራፎ ያለበት የመታወቅያ ወረቀትና ወቅታዊ ስሞና ኣድራሻዎ ያለበት ዶኩሜንት
የተፈቀዱ የፎቶግራፍ መታወቅያ ወረቀቶች (ኣንዱን ይምረጡ)
ግዜው ያለፈ ሊሆን ይችላል
የተፈቀዱ የፎቶግራፍ መታወቅያ ወረቀቶች (ኣንዱን ይምረጡ)
በኤሌክትሮኒክ መሳርያም ለማሳየት ይቻላል
3. የቤትዎን ኣድራሻ በትክክል የሚመሰክር የተመዘገበ መራጭ
በኣካባቢዎ የሚኖር፡ ለመምረጥ የተመዘገበ ሰው፡ ከእርሶ ጋር ኣብሮ ወደ ምርጫው ጣብያ በመሄድ በሰጡት የቤት ኣድራሻ ውስጥ እንደሚኖሩ በመሃላ ሊያረጋግጥሎ ይችላል። ለእርሶ ሌላ የተመዘገበ መራጭ ከመሰክረሎ ግን እርስዎ ለሌላ ሊመስክሩ ኣይችሉም።
4. በኮሌጅ የሚኖሩ የተማሪዎች ስም ዝርዝር
ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ፡በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚኖሩ የተማሪዎቻቸውን የስም ዝርዝር ለኣስመራጭ ኮሚቴ ባለስልጣኖች ይልካሉ።በዚህ ዝርዝር ውስጥ ስምዎ ካለ፡ ስዕሎ ያለበትን የኮሌጅ መታወቅያ ወረቀትዎን በማሳየት ምዝገባዎን ያጠናቅቁ።
5. በኣካባቢው የሚካሄድ ህጋዊ ምዝገባ
በኣንድ ኣካባቢ ለመምረጥ ከተመዘገቡ በውሃላ፡ በዛው ኣካባቢ ኣድራሻዎን ወይም ስሞን ከቀየሩ፡ የቀድሞ ስሞንና ኣድራሻዎን ብቻ ነው ለኣስመራጭ ኮሚቴው ዳኛ መንገር ያለቦ።
6. ዘግይቶ ስለመመዝገብ የተሰጠ ማስታወቅያ
ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ባሉት 20 ቀናት ውስጥ እመርጣለሁ ብለው ከተመዘገቡ፡ ዘግይቶ የመመዝገብ ማስታወቅያ በፖስታ ሊደርስዎ ይችል ይሆናል። ይህንን የደረስዎትን ማስታወቅያ ወደምርጫው ጣብያ ይዘው በመሄድ እንደ ኣንድ የመኖርያ ቤት ማረጋገጫ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።
7. የጋራ መኖርያ ቤቶች የኣስተዳደር ክፍል ባለስልጣን
በጋራ መኖርያ ቤቶች የሚቀመጡ ከሆነ፡ የመኖርያ ቤቶቹ የኣስተዳደር ባለስልጣን ከእርስዎ ጋር ወደ ምርጫው ጣብያ በመሄድ የሚኖሩበትን ኣድራሻ ሊያረጋግጥልዎ ይችላል።ይህም "ቫውቺንግ" በመባል ይታወቃል።ይሂው የኣስተዳደር ክፍል ባለስልጣን ለእያንዳንዱ ተቀማጭ ምስክርነቱን ሊሰጥ ይችላል።